ስፓርት

ሲዳማ ቡና እና አርባምንጭ ከተማ የቅጣት ውሳኔ ተላለፈባቸው

By Mikias Ayele

October 17, 2022

በሦስተኛ ሣምንት ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች ላይ ተስተውለዋል ያላቸውን የሥነ ምግባር ግድፈቶች ተከትሎ ነው የሊግ ኩባንያው የዲስፕሊን ኮሚቴ የቅጣት ውሳኔዎችን ያሳለፈው፡፡

በዚህም ሲዳማ ቡና በቅዱስ ጊዮርጊስ በተሸነፈበት ጨዋታላይ የክለቡ ደጋፊዎች የዕለቱን ዳኛ አፀያፊ ስድብ ተሳድበዋል የሚል ሪፖርት በመቅረቡ በክለቡ ላይ የ50 ሺህ ብር የገንዘብ ቅጣት ተላልፏል፡፡

በተጨማሪም አርባምንጭ ከተማ መቻልን በረታበት ጨዋታ የአርባምንጩ ግብ ጠባቂ አቤል ማሞ የተመዘገበ የመለያ ቁጥሩ 1 ሆኖ ሳለ 99 ቁጥር ለብሶ በመግባቱ ክለቡ የ6 ሺህ ብር የገንዘብ ቅጣት እንዲከፍል ተወስኖበታል መባሉን የሊግ ኩባንያው መረጃ ያመላክታል፡፡