የሀገር ውስጥ ዜና

በሞጆ ከተማ 51 ቦምብ ከ4 ተጠርጣሪ ዎች ጋር በቁጥጥር ስር ዋለ

By Amele Demsew

October 16, 2022

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 6 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በምስራቅ ሸዋ ዞን ሞጆ ከተማ በህገ ወጥ መንገድ ሲጓጓዝ የነበረ 51 ቦምብ ከአራት ተጠርጣሪ ዎች ጋር በቁጥጥር ስር ዋለ፡፡

ህገ ወጥ ቦንቦቹ ዛሬ ከንጋቱ 11ሰዓት ጀምሮ በተደረገ የመረጃ ክትትል ሞጆ ከተማ ላይ መያዛቸውን የደኅንነት ምንጮች አመልክተዋል፡፡

ቦምቡን ሲያጓጉዙ ነበር የተባሉ አራት ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውም ነው የተገለጸው፡፡