Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የሕዝብ መሰረታዊ ፍላጎት የሚሟላው ገቢ በአግባቡ ሲሰበሰብ ነው- ም/ርዕሰ መስተዳድር ነጋሽ ዋጌሾ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 5፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የሕዝብን መሰረታዊ ፍላጎት ማሟላት የሚቻለው ገቢን በአግባቡ መሰብሰብ ሲቻል ነው ሲሉ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ም/ርዕሰ መስተዳድር ነጋሽ ዋጌሾ ተናገሩ፡፡

የክልሉ ገቢዎች ቢሮ በ2014 ዓ.ም አፈፃጸምና በ2015 ዕቅድ ላይ የውይይት መድረክ እያካሄደ ነው፡፡

የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ነጋሽ ዋጌሾ በመድረኩ ላይ ባደረጉት ንግግር÷ የሕዝቦችን መሰረታዊ ፍላጎት ማሟላት የሚቻለው ካለው ሀብት ላይ ገቢን በአግባቡ መሰብሰብ ሲቻል መሆኑን በአጽንኦት ገልጸዋል፡፡

የተሻለ ገቢ መሰብሰብም በቴክኖሎጂ የታገዘ ዘመናዊ የታክስ አሰባሰብ ስርዓት መዘርጋት እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡

የገቢዎች ሚኒስትር ዴኤታ መሰረት መስቀሌ እንደገለጹት÷ ሀገራዊ ወጪን በራስ ገቢ መሸፈን የሚያስችል ኢኮኖሚ መገንባት ወሳኝ ነው፡፡

በ2014 ዓ.ም በክልሉ ከ2 ነጥብ 8 ቢሊየን ብር በላይ ለመሰብሰብ ታቅዶ ከ3 ቢሊየን ብር በላይ መሰብሰብ መቻሉም በውይይቱ ላይ ተገልጿል፡፡

በ2015 ከመደበኛ ግብር፣ ቀጥተኛ ከሆኑና ቀጥተኛ ካልሆኑ ታክሶች እንዲሁም ታክስ ካልሆኑ ገቢዎች ከ4 ቢሊየን ብር በላይ ለመሰብሰብ ታቅዷል፡፡

በተስፋዬ ምሬሳ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version