አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 4 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በበጀት ዓመቱ የመጀመሪያ ሩብ ዓመት ለ799 ባለሃብቶች አዲስ የኢንቨስትመንት ፈቃድ መሰጠቱ ተገልጿል፡፡
የአዲስ አበባ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ዋና እና ምክትል ኮሚሽነሮች የኮሚሽኑ ዳይሬክተሮች እና የቡድን መሪዎች የመጀመሪያ ሩብ ዓመት ዕቅድ አፈጻጸምን ገምግመዋል፡፡
ኮሚሽኑ በመጀመሪያው ሩብ ዓመት የዝግጅት ምዕራፍ ሥራዎች ለ799 ባለሃብት አዲስ ፈቃድ፣ ለ38 ፕሮጀክቶች ማስፋፊያ፣ ለ96 ፕሮጀክቶች ለውጥ ፣ ለ24 ፕሮጀክቶች ምትክ እንዲሁም ለ430 ፕሮጀክቶች የዕድሳት አገልግሎት መስጠቱ ተመላክቷል፡፡
ከዚህ ባለፈም ኮሚሽኑ ፕሮጀክቶች ላይ የክትትልና ድጋፍ ሥራዎች ላይ ለ107 ፕሮጀክቶች ክትትል በማድረግ 374 ቋሚ የሥራ ዕድል የፈጠረ ሲሆን÷ 50 ፕሮጀክቶች ደግሞ ወደ ማምረት መሸጋገራቸው ተጠቁሟል፡፡
በተጨማሪም 175 የካፒታል ዕቃ 11 የግንባታ ዕቃዎች 80 ተሽከርካሪ 10 መለዋወጫ 25 የግብር ዕፎይታ መፍቀዱን በግምገማ መድረኩ ተነስቷል፡፡
የአዲስ አበባ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ግርማ ሰይፉ÷ወደ ኮሚሽኑ የሚመጡ ባለሃብቶች በአገልግሎቱ ረክተው ለሀገራቸው እንዲያስቡ ቀልጣፋ እና አስደሳች አገልግሎት መስጠት እንደሚገባ መጠቆማቸውን ከኮሚሽኑ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!