Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የሰላም ሚኒስቴር አመራሮችና ሰራተኞች በአዲስ አበባ ላንበረት መነኻሪያ ተገኝተዉ የኮሮና ቫይረስ የመከላከል ስራ አከናወኑ

አዲስ አበባ፣መጋቢት 13፣2012(ኤፍ.ቢ፣.ሲ)የሰላም ሚኒስቴር አመራሮችና ሰራተኞች በአዲስ አበባ ላንበረት መነኻሪያ ተገኝተዉ የኮሮና ቫይረስ የመከላከል ስራ አከናውነዋል፡፡

በዚህ ተግባር ላይ የሰላም ሚኒስቴር  ሚኒስትር ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚልን ጨምሮ የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ አመራሮችና ሰራተኞች  መገኘታቸው ተገልጿል፡፡

የሚኒስቴሩ አመራሮችና ሰራተኞች ለመንገደኞች እጅ የማስታጠብ ፣ የሳይነተሪ ዕደላ እና የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎችን  ማከናወናቸው ነው የተገለጸው፡፡

የሰላም ሚኒስትር ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል ኢትዮጵያዊያን ከተባበርንና ተጋግዘን ከሰራን የማንሻገረዉ ችግር፣ የማንፈታዉ ፈተና የለም ብለዋል ።

አያይዘውም አሁን በአገር ደረጃ የተፈጠረዉን የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ለመከላከል ሁላችንም ትኩረት ሰጥተን ሳንረበሽና ሳንደናገጥ ተገቢዉን ጥንቃቄ በማድረግ ችግሩን ማለፍ  እንችላለን  ማለታቸውን ከሰላም ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

 

Exit mobile version