Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

አፍሪካውያን ወጣቶች በኢትዮጵያ የዲጂታልና ቴክኖሎጂ የኢንቨስትመንት ዘርፍ እንዲሳተፉ ጥሪ ቀረበ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 3፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በሩዋንዳ የኢትዮጵያ አምባሳደር ዳባ ደበሌ በሩዋንዳ በተካሄደው የአፍሪካ ወጣቶች ጉባዔ ላይ ተሳትፈዋል።

በሩዋንዳ እየተካሄደ ያለው የአፍሪካ ወጣቶች ጉባዔ ጎን ለጎን አምባሳደር ለተለያዩ የአፍሪካ ወጣቶችና ለጉባዔው ተሳታፊዎች ስለኢትዮጵያ የዲጂታል ኢኮኖሚና በቴክኖሎጂ መስክ ያሉ የኢንቨስትመንት አማራጮች ዙሪያ ገለጻ አድርገዋል።

ኢትዮጵያ ለዘርፉ ቀዳሚ ትኩረት የሰጠች በመሆኗ ወጣቶች ተሳትፎ እንዲያደርጉም ነው ጥሪ ያቀረቡት፡፡

አምባሳደር ዳባ ፥ ኢትዮጵያ የአፍሪካ ወጣቶች ለአህጉሪቷ እድገት መሠረት እንደሆኑ በማመን ልዩ ትኩረት ሰጥታ እየተንቀሳቀሰች ነው ብለዋል።

በአፍሪካ ዘላቂ ሰላምና መረጋጋት እንዲፈጠር እንዲሁም የአየር ንብረት ለውጥን በመከላከል ረገድ የወጣቶች ሚና የጎላ እንደሆነም ነው የገለጹት፡፡

በጉባዔው ላይ የተሳተፉ በርካታ የዲፕሎማሲው ማኅበረሰብ አባላት ኢትዮጵያ በቅርቡ መርቃ የከፈተችው የሳይንስ ሙዚየምን ማድነቃቸውን አምባሳደር ዳባ ተናግረዋል።

ጉባዔው የአፍሪካ ወጣቶች ላይ በመስራት የተሻለች አህጉር መፍጠር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ አተኩሮ እየተካሄደ መሆኑን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version