አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 3፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ አረንጓዴ ልማት ዲፕሎማሲ የወጣቶች ልዑክ ኬንያ ናይሮቢ ገብቷል፡፡
የልዑካን ቡድኑ አባላት ኬንያ ሲደርሱ በኬንያ የኢትዮጵያ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ባጫ ደበሌ የእንኳን ደህና መጣችሁ አቀባበል አድርገውላቸዋል፡፡
በጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ማዕከል አስተባባሪ ዶክተር ቢቂላ ሁሪሳ በዚህ ወቅት እንዳሉት÷ የመጣነው ችግኝ ለመትከል ብቻ ሳይሆን ወንድማማችነትን ለመትከል ነው ብለዋል፡፡
ዓለምን እየፈተነ ያለው የአየር ንብረት ለውጥ ኢትዮጵያ ብቻ በምታካሂደው የአረንጓዴ አሻራ ርብርብ መካላከል ስለማይቻል አፍሪካውያን እርስ በርስ ተሳስረው ሊስሩ እንደሚገባ አንስተዋል፡፡
የልዑካን ቡድኑ አባላት በነገው ዕለት በዋና ከተማዋ ናይሮቢ ከሀገሪቱ ከፍተኛ ባለስልጣናት ጋር በመሆን ችግኞችን እንደሚተክሉ ከብልጽግና ፓርቲ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡