Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በፕሪሚየርሊጉ ቅዱስ ጊዮርጊስ ሲዳማ ቡናን 5 ለ 1 አሸነፈ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 3፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ቅዱስ ጊዮርጊስ ሲዳማ ቡናን 5 ለ 1 በሆነ ውጤት በማሸነፍ መሪነቱን አጠናክሯል፡፡

በባህርዳር ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ ኢስማኤል ኦሮ አጉሮ ሀትሪክ ሲሰራ÷ በረከት ወልዴ እና አማኑኤል ገብረሚካኤል የጊዮርጊስን የማሸነፊያ ግቦች አስቆጥረዋል፡፡

ፈረሰኞች ሲዳማ ቡናን ማሸነፋቸውን ተከትሎ በ9 ነጥብ መሪነታቸውን አጠናክረዋል፡፡

በተመሳሳይ ወላይታ ዲቻ እና ኢትዮኤሌክትሪክ  በዛሬው ዕለት ያደረጉት ጨዋታ አንድ አቻ  በሆነ ውጤት ተጠናቋል፡፡

Exit mobile version