Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የፌዴሬሽን ምክር ቤት የቀረበውን የ2015 በጀት ዓመት እቅድ አጸደቀ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 1፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የፌዴሬሽን ምክር ቤት የድጎማና የጋራ ገቢዎች ድልድል ጉዳይ ቋሚ ኮሚቴ ያቀረበውን የ2015 በጀት ዓመት እቅድ ተወያይቶ አጸደቀ፡፡

የፌዴሬሽን ምክር ቤት ስድስተኛ የፓርላማ ዘመን፣ 2ኛ ዓመት የሥራ ጊዜ፣ 1ኛ መደበኛ ስብሰባውን አካሂዷል፡፡

ከምክር ቤት አባላት እቅዱን አስመልክቶ የተለያዩ ጥያቄዎችና አስተያየቶች ቀርበው የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ አቶ ሽመልስ አብዲሳ ምላሽ ሰጥተዋል፡፡

በተለይም የፌዴራል ሥርዓቱ ዋናው መሠረት የፊሲካል ፌዴራሊዝም መሆኑን ጠቁመው ፥ ቋሚ ኮሚቴው ከሃብት ክፍፍሉ ጋር በተያያዘ ካሁን በፊት የነበሩ ችግሮችን በጥናት በመለየት ለመቅረፍ እየሠራ ቢሆንም ችግሩን ከመሠረቱ ለመፍታት ግን የሕዝብና ቤት ቆጠራ ማካሄድ ይገባል ነው ያሉት።

ሰብሳቢው አክለውም ፥ ቀመሩን ለመሥራት ቆጠራው ዋነኛው ጉዳይ እንደሆነ አስታውቀው ፥ ያሉብን ሀገራዊ ችግሮች በቶሎ ተቀርፈው ቆጠራው እስከሚካሄድ ድረስ ቋሚ ኮሚቴው ለቆጠራው አስፈላጊ የቅድመ ዝግጅት ሥራ እየሠራ መሆኑን አስገንዝበዋል።

አቶ ሽመልስ የመሠረተ ልማቱን ፍትሐዊነት በተመለከተ ለቀረበው ጥያቄ ሲያብራሩ ቀደም ሲል በክልሎች መካከል ፍትሐዊነት የጎደለው አፈጻጸም እንደነበር መግለጻቸውን ከምክር ቤቱ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ችግሩን በአንድ ጊዜ መሻገር ስለማይቻል በሚቀጥሉት ዓመታት ችግሩን ለማቃለል እንደሚሠራና በዚህ ዘርፍ የፕሮጀክት አፈጻጸም መጓተት፣ የበጀት እጥረትና ችግሮችን በአንድ ጊዜ እንዲፈቱ የመፈለግ አዝማሚያ ተግዳሮቶች በመሆናቸው በእነዚህ ላይ ትኩረት ሰጥቶ መሥራት እንደሚገባም አስገንዝበዋል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version