አዲስ አበባ፣ መስከረም 30፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) 6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤትና የፌዴሬሽን ምክር ቤት 2ኛ ዓመት የስራ ዘመን መክፈቻ ስነ-ስርዓት ዛሬ ይካሄዳል።
ሁለቱ ምክር ቤቶች ባለፈው 2014 ዓ.ም የ1ኛ ዓመት የስራ ዘመናቸውን አጠናቀው በ2015 ዓ.ም የ2ኛ ዓመት የስራ የዘመናቸውን የሚይዙ ይሆናል፡፡
በዚህም 6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤትና የፌዴሬሽን ምክር ቤት 2ኛ ዓመት የስራ ዘመን የጋራ መክፈቻ ሥነ-ስርዓት ዛሬ መስከረም 30 ቀን 2015 ዓ.ም ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ በተገኙበት ከቀኑ 8፡30 ጀምሮ ይካሄዳል፡፡
በመክፈቻ ስነ-ስርዓቱ ላይ ፕሬዚዳንቷ የመንግስት ዕቅድን በሚመለከት ለሁለቱ ምክር ቤቶች ንግግር ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል።
በመርሐ ግብሩ የተለያዩ ሀገራት አምባሳደሮች፣ የዓለም አቀፍ ተቋማት ተጠሪዎች፣ የሃይማኖት አባቶችና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች እንደሚገኙ ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡