ዓለምአቀፋዊ ዜና

በዩክሬን ዋና ከተማ ኪየቭ የሚሳኤል ጥቃት መድረሱ ተሰማ

By Meseret Awoke

October 10, 2022

አዲስ አበባ፣ መስከረም 30፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በዩክሬን ዋና ከተማ ኪየቭ የሚሳኤል ጥቃት መድረሱን የሀገሪቱ ከፍተኛ ባለስልጣናት ገለጹ፡፡

የኪየቭ ከንቲባ ቪታሊ ክሊሺኮ በማዕከላዊ ኪየቭ “ከሩሲያ የተተኮሰ ሚሳኤል ጉዳት አድርሷል” ብለዋል።

የሚሳኤል ጥቃቱ የዩክሬን የደህንነት አገልግሎት መስሪያ ቤት በሚገኝበት ቭላድሚርስካያ አካባቢ ጉዳት መድረሱን የዩክሬን የሀገር ውስጥ ሚኒስትር አማካሪ አንቶን ጌራሺቸንኮ ገልጸዋል።

ከዚህ ባለፈም በኔፐር እና ልቪቭ ከተሞች ጥቃት መፈጸሙን ምንጮችን ዋቢ ያደረገው የአር ቲ ዘገባ ያመላክታል።

ከክሬሚያ የሚያገናኘው እና ሩሲያ በኢኮኖሚም ሆነ በማህበራዊም ቁልፍ ነው የምትለው ድልድይ በከባድ ተሽከርካሪ ላይ በተጠመደ ፈንጅ መመታቱ ይታወሳል።

ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲንም የዩክሬን የደህንነት አገልግሎት መስሪያ ቤት ከፍንዳታው ጀርባ አለበት በማለት ዩክሬንን በአሸባሪነት ፈርጀዋታል።

ከድልድዩ ፍናዳት በኋላም ሌሊቱን በማዕከላዊ ኪየቭ የሚሳኤል ጥቃት ተፈጽሟል ነው የተባለው፡፡

ስለ ጥቃቱ ከሩሲያ በኩል የተባለ ነገር ባይኖርም ዩክሬን ግን ሞስኮን ተጠያቂ አድርጋለች።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!