Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ የንግድና ኢንቨስትመንት ምድብ ችሎት በይፋ ስራ ጀመረ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 29፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ)በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ የንግድና ኢንቨስትመንት ምድብ ችሎት ይፋዊ ስራ የማስጀመሪያ መርሃ ግብር ዛሬ ተካሂዷል።

የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ለመጀመሪያ ጊዜ በአይነቱ ልዩ የሆነ የንግድና ኢንቨስትመንት ምድብ ችሎትን አቋቁሞ አገልግሎት መስጠት ጀምሯል።

በማስጀመሪያ መርሃ ግብሩ ላይ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈጉባኤ ታገሰ ጫፎ፣የጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት መዓዛ አሸናፊ፣የጠቅላይ ፍርድ ቤት ምክትል ፕሬዚዳንት ሰለሞን አረዳ እና ሌሎች ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

ችሎቱ በአዲስ አበባ አራዳ ክፍለ ከተማ የቀድሞው ብሪቲሽ ካውንስል ህንጻ ላይ ነው ስራ የጀመረው።

ከንግድ እና ኢንቨስትመንት ጋር ተያያዥነት ያላቸውን የንግድ፣ የባንክ፣የኢንሹራንስ እና የኮንስትራክሽን የፍርድ ክርክሮች የሚስተናገዱበት ነው ተብሏል።

ከዚህ በፊት በአስተዳደራዊ ጉዳዮች ላይ ተደራጅተው ሲታዩ የነበሩ ጉዳዮችን በዘርፍ በመለየት ልዩ ችሎት መጀመሩም ለፍርድ ሂደቱ የራሱ አዎንታዊ ሚና እንደሚኖረው መገለፁን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

Exit mobile version