የሀገር ውስጥ ዜና

ወ/ሮ ዳግማዊት ሞገስ ከናይጄሪያ፣ ኳታር፣ ከደቡብ ኮሪያ እና ከሳዑዲ ዓረቢያ አቻዎቻቸው ጋር ተወያዩ

By Shambel Mihret

October 07, 2022

አዲስ አበባ፣ መስከረም 27፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ዳግማዊት ሞገስ ከናይጄሪያ፣ ኳታር፣ ከደቡብ ኮሪያ እና ከሳዑዲ ዓረቢያ የትራንስፖርት ሚኒስትሮች ጋር ተወያይተዋል፡፡

በካናዳ ሞንትሪያል እየተካሄደ በሚገኘው 41ኛው ዓለም አቀፍ የሲቪል አቬየሽን ጉባዔ ላይ በሚኒስትሯ የተመራ ልዑክ ኢትዮጵያን በመወከል እየተሳተፈ ነው፡፡

ወይዘሮ ዳግማዊት ሞገስ ከጉባኤው ጎን ለጎን በትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ዘርፍ ከናይጄሪያ፣ ኳታር፣ ከደቡብ ኮሪያ እና ከሳዑዲ ዓረቢያ አቻዎቻቸው ጋር መክረዋል፡፡

የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ዘርፍ የሚፈጥረውን መልካም የሀገራት ትስስር በማጠናከር ዙሪያ በመምከር በጋራ ለመስራት ከስምምነት ላይ መድረሳቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡