የሀገር ውስጥ ዜና

ግጭቱን ለመፍታት መንግሥት የሚወስዳቸውን ሁሉንም ዓይነት የመፍትሔ እርምጃዎች አጠናከሮ ይቀጥላል – የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት

By ዮሐንስ ደርበው

October 05, 2022

አዲስ አበባ ፣ መስከረም 25 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ግጭቱን ለመፍታት መንግሥት ሲወስዳቸው የቆያቸውን ሁሉንም ዓይነት የመፍትሔ እርምጃዎች አጠናከሮ እንደሚቀጥል የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት አስታወቀ።

አገልግሎቱ ባወጣው የወቅታዊ ሁኔታ መረጃ የአፍሪካ ኅብረት የሰላም ንግግሩን የሚመሩ አካላትን፣ ቀንና ስፍራን አሳውቆ የሰላም ውይይቱ እንዲጀመር ይፋዊ ጥሪ ማቅረቡን አስታውቋል።