የሀገር ውስጥ ዜና

የአልሸባብ ከፍተኛ አመራር የሆነው አብዱላሂ ያሬ ተገደለ

By Mikias Ayele

October 03, 2022

አዲስ አበባ፣ መስከረም 23፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአልሸባብ ከፍተኛ አመራር የሆነው አብዱላሂ ያሪ በተወሰደበት የድሮን ጥቃት መገደሉን የሶማሊያ መንግስት አስታወቀ፡፡

የሶማሊያ የማስታወቂያ ሚኒስቴር እንደገለጸው የአልሸባብ መስራች እንደሆነ የሚታመነው አብዱላሂ ያሬ በሶማሊያ ሀራምካ የባህርዳርቻ አካባቢ በተወሰደበት የተቀናጄ የአየር ጥቃት ተገድሏል፡፡

ግለሰቡ የቀድሞው የሹራ ምክር ቤት ሃላፊ እና የአልሸባብ የፋይናንስ ዳይሬክተር እንደነበርም ነው የተገለፀው፡፡

እንደሚኒስቴሩ ገለፃ የአልሸባብ መሪ መገደሉ ለሶማሊያ ሰላም እና ደህንነት መጠበቅ እንዲሁም ለቡድኑ መዳከም ከፍተኛ አስተዋፅኦ ይኖረዋል፡፡

በአልሸባብ ላይ እየተወሰደ ያለው እርምጃ ፕሬዚዳንት ሀሰን ሼክ ሞሀሙድ በአክራሪዎች ላይ ሁሉን አቀፍ እርምጃ እንደሚወስዱ ቃል መግባታቸውን ተከትሎ የተወሰደ መሆኑን አል አረቢያ ዘግቧል፡፡