አዲስ አበባ፣ መስከረም 23፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢንዱስትሪ ሚኒስቴርና ተጠሪ ተቋማቱ ለመከላከያ ሠራዊት 16 ሚሊየን ብር የሚገመት የዓይነት ድጋፍ አደረጉ።
ድጋፉ የምግብ፣ መድሐኒትና የተለያዩ ቁሳቁስን ያካተተ ነው።
የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ አቶ መላኩ አለበል በዚህ ወቅት ፥ ድጋፉ መከላከያ ሠራዊት እየከፈለ ያለውን እዳ ለመክፈልና ደጀንነት ለማረጋጥ ያለመ ነው ብለዋል።
ድጋፉ የህይወት መስዋዕትነት እየከፈለ ላለው ጀግናው የመከላከያ ሠራዊት በድጋፍ መልክ ሳይሆን በግዴታ የሚሰጥ ነው ያሉ ሲሆን ፥ ሠራዊቱ እየከፈ ላለው ዋጋም ምስጋና አቅርበዋል።
በተጨማሪም ለሠራዊቱ የሚሆኑ አልባሳትን በሀገር ውስጥ በጥራት እንዲመረቱ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን ጠቅሰው፥ ሚኒስቴሩ መከላከያን የሚያጠናክሩ ስራዎችን እየሰራ መሆኑንም ነው ያነሱት።
ድጋፉን የተረከቡት የመከላከያ ሚኒስትር ዴኤታ ማርታ ሉዊጂ ፥ ለጀግናው መከላከያ ሠራዊት የተደረገው የዓይነት ድጋፍ ሰራዊቱ የሚያጠናክር ነው ብለዋል፡፡
ለሠራዊቱ የሚቀርቡ ግብዓቶች በሀገር ውስጥ እንዲመረቱ ከኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ጋር በጋራ እየተሰራ መሆኑንም ነው የገለጹት።
ሚኒስትር ዴኤታዋ አክለውም ፥ ሁሉም በተሰማራበት ለሠራዊቱ በደጀንነት ሊቆም እንደሚገባው ተናግረዋል።
በትዕግስት ብርሃኔ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!