አዲስ አበባ፣ መስከረም 23፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የባህልና ስፖርት ሚኒስትር አቶ ቀጄላ መርዳሳ በቀጣይ የሁለቱ ሀገራት ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነቶች በሚጠናከሩበት ጉዳዮች ዙሪያ ከሩዋንዳ አምባሳደር ጋር ተወያይተዋል፡፡
ሚኒስትሩ በኢትዮጵያ የሩዋንዳ አምባሳደር ሆፕ ቱሙኩነድን በጽህፈት ቤታቸው ተቀብለው ባነጋገሩበት ወቅት የኢትዮጵያና ሩዋንዳ ህዝብን መሰረት ያደረጉ የባህል ትሥሥር በሚጠናከርበት ዙሪያም መክረዋል፡፡
በውይይቱ ሁለቱ ሀገራት የጋራ የሚያደርጓቸው በርካታ እሴቶች እንዳሏቸው መገለፁን ከባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
አምባሳደሯ በቅርቡ ሩዋንዳ ኪጋሊ በሚካሄደው የአፍሪካ ወጣቶች ኮንፍረንስ ላይ ኢትዮጵያ እንድትሳተፍ የግብዣ ደብዳቤም ለሚኒስትሩ አስረክበዋል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!