የሀገር ውስጥ ዜና

ከኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ከ1 ነጥብ 5 ሚሊየን ዶላር በላይ ተሰባሰበ

By ዮሐንስ ደርበው

October 03, 2022

አዲስ አበባ፣ መስከረም 23፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) መንግሥት ያቀረበውን ሀገራዊ ጥሪ ተከትሎ በውጭ ከሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ከ1 ነጥብ 5 ሚሊየን ዶላር በላይ መሰብሰቡን የኢትዮጵያ ዳያስፖራ አገልግሎት አስታወቀ፡፡

ገንዘቡ የተሰበሰበው መንግሥት ያቀረበውን ሀገራዊ ጥሪ ተከትሎ ባለፉት ሁለት ሳምንታት በኢፌዴሪ ሚሲዮኖች አስተባባሪነት በተከናወነ የሀብት ማሰባሰብ ሂደት ነው፡፡