አዲስ አበባ፣ መስከረም 23፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) መንግሥት ያቀረበውን ሀገራዊ ጥሪ ተከትሎ በውጭ ከሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ከ1 ነጥብ 5 ሚሊየን ዶላር በላይ መሰብሰቡን የኢትዮጵያ ዳያስፖራ አገልግሎት አስታወቀ፡፡
ገንዘቡ የተሰበሰበው መንግሥት ያቀረበውን ሀገራዊ ጥሪ ተከትሎ ባለፉት ሁለት ሳምንታት በኢፌዴሪ ሚሲዮኖች አስተባባሪነት በተከናወነ የሀብት ማሰባሰብ ሂደት ነው፡፡
ከተሰበሰበው ገንዘብ ውስጥ 1 ነጥብ 4 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር፣ 59 ነጥብ 3 ሺህ ዩሮ እንዲሁም 53 ሺህ ፓውንድ መሆኑን እና 35 ሺህ የአሜሪካ ዶላር እና 8 ሺህ ዩሮ ቃል መገባቱንም ነው አገልግሎቱ ያስታወቀው፡፡
በዚሁ ጊዜ ከ8 ሚሊየን ዶላር በላይ ግምት ያለው ቁሳቁስ መሰባሰቡም ታውቋል።
የኢትዮጵያ ዳያስፖራ አገልግሎት በአጭር ጊዜ ውስጥ ለተሰባሰበው ሀብት አመስግኗል፡፡
በሚሲዮኖች አስተባባሪነት በኢፌዲሪ የገንዘብ ሚኒስቴር በተዘጋጁት አካውንት ቁጥሮች ማለትም ለዩሮ (1000439142832)፣ ለዶላር (1000439142786) እንዲሁም ለፓውንድ (1000443606304) በመጠቀም ከሚያደርገው ድጋፍ በተጨማሪ የአይዞን ኢትዮጵያ ቴክኖሎጂ አማራጭን (https://eyezonethiopia.com) በመጠቀም ዳያስፖራው ድጋፉን አጠናክሮ እንዲቀጥል አገልግሎቱ ጥሪ አቅርቧል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!