አዲስ አበባ፣ መስከረም 23፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የፌዴራል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን ሀገራዊና ተቋማዊ ኃላፊነታቸውን በብቃት ለተወጡና የላቀ አፈፃፀም ላስመዘገቡ አመራሮች፣ አባላትና ሰራተኞች ዕውቅና እየሰጠ ነው፡፡
በመርሐ ግብሩ ከፍተኛ የስትራቴጂክ አመራሮች፣ ልዩ የስፖርት ተሸላሚዎች፣ የክልል ማረሚያ ቤቶች፣ የአድማ መቆጣጠር፣ ልዩ እጀባ፣ የሙዚቃና ቲአትር ቡድንና ግለሰቦች ይሾማሉ ፤ ይሸለማሉ ተብሎ ይጠበቃል።
በማበረታቻ እና ዕውቅና መርሐ ግብሩ በአትሌቲከሱ ላበረከቱት የላቀ አስተዋፆ ለአትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ኮ/ር አትሌት ደራርቱ ቱሉ እና በርካታ ጀግኖች አትሌቶችን ላፈሩት አንጋፋው አሰልጣኝ ኮ/ር ሁሴን ሼቦ በረዳት ኮሚሽነርነት ማዕረግ ተሹመዋል።
በመርሐ ግብሩ የመከላከያ ሚኒስትሩ አብርሃም በላይ፣ የገንዘብ ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር እዮብ ተካልኝ ፣ የፌዴራል ማረሚያ ቤት ኮሚሽነር ጄኔራል ዳመና ዳሮታ፣ የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት መዓዛ አሸናፊ፣የፍትህ ሚኒስትሩ ዶክተር ጌዴዎን ጢሞቲዎስ፣ የህግ ፍትህ ዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ወይዘሮ እጸገነት መንግስቱና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።
የፌዴራል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን ከተሰጠው ተልዕኮ ጎን ለጎን ሀገር ተገዳ ወደ ጦርነት በገባች ወቅት በዱር በገደሉ እየተዋደቀ ታሪካዊ ጀብዱ እየሰራ ለሚገኘው የሀገር መከላከያ ሠራዊት የገንዘብና የዓይነት ድጋፍ ከማድረጉም ባሻገር በአስፈላጊው ጊዜ ከሠራዊቱ ጎን መሆኑ በመድረኩ ተነስቷል፡፡
በእምነት ዘላለም
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!