Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በለንደን እና ጣልያን በተካሄዱ የተለያዩ የሩጫ ውድድሮች ኢትዮጵያ አሸነፈች

አዲስ አበባ፣ መስከረም 22፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በለንደን የማራቶን፣ በጣልያን የግማሽ ማራቶን እና የ10 ኪሎ ሜትር የሩጫ ውድድሮችን ኢትዮጵያ በበላይነት አጠናቀቀች፡፡

በለንደን የተካሄደው የሴቶች የማራቶን ውድድር በአትሌት ያለምዘርፍ የኋላው አሸናፊነት ፍጻሜውን አግኝቷል፡፡

አትሌት ያለምዘርፍ እርቀቱን 2 ሰዓት ከ17 ደቂቃ ከ25 ሰከንድ በሆነ ሰዓት በመግባት ነው ያሸነፈችው፡፡

በለንደን በተካሄደ የወንዶች የማራቶን ውድድር ደግሞ÷ አትሌት ልዑል ገብረ ሥላሴ ሁለተኛ እንዲሁም አትሌት ቀነኒሳ በቀለ አምሥተኛ በመሆን ውድድሩን አጠናቀዋል፡፡

እንዲሁም በጣልያን በተካሄደ የግማሽ ማራቶን ውድድር የዓለም ሻምፒዮኑ አትሌት ታምራት ቶላ የቦታውን ሰዓት በማሻሻል ጭምር አሸንፏል፡፡

በተመሳሳይ በሴቶች አትሌት ብሩክታይት ደገፋው አሸንፋለች፡፡

በወንዶች በተካሄደ የ10 ኪሎ ሜትር ውድድር ደግሞ አትሌት ሙክታር ኢድሪስ ማሸነፉን የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን መረጃ አመላክቷል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version