Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በቢሾፍቱ የሆረ ሀርሰዴ የኢሬቻ በዓል መከበር ጀመረ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 22፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በቢሾፍቱ የሆረ ሀርሰዴ የኢሬቻ በዓል እየተከበረ ይገኛል፡፡

በአሁኑ ሰዓት የበዓሉ ተካፋዬች በአባገዳዎች እና ሀደሲንቄዎች እየተመሩ ወደ ሆረ ሃርሰዴ ሐይቅ በማምራት ላይ ናቸው።

አባገዳና ሃደሲንቄዎች በእጃቸው እርጥብ ሳር በመያዝ ከጨለማ ወደ ብርሃን መሸጋገርን በማብሰር መልካም ምኞታቸውን እየገለፁ ፥ ወጣቶች ባህላዊ ጭፈራዎችን እያሰሙ እየተጓዙ ነው።

የፀጥታ ሃይሎች ከህብረተሰቡ ጋር በመቀናጀት በዓሉ በሰላም እንዲከበር እየሰሩ ነው።

ኢሬቻ በኦሮሞ ህዝብ ዘንድ ትልቅ ቦታ የሚሰጠው የገዳ ስርዓት መገለጫ ሲሆን ፥ በርካቶችም ይህንኑ በዓል በቢሾፍቱ እየተካፈሉ ይገኛሉ።

በሀብታሙ ተ/ስላሴ

ምስል በአብርሃም ፈቀደ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version