Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የኢሬቻ በዓል ያለምንም የፀጥታ ችግር እንዲጠናቀቅ ቅድመ ዝግጅት ተጠናቋል

አዲስ አበባ፣ መስከረም 20፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢሬቻ በዓል ያለምንም የፀጥታ ችግር እንዲጠናቀቅ ቅድመ ዝግጅት መጠናቀቁን የኦሮሚያ ክልል አስተዳደርና ፀጥታ ቢሮ እና የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቁ፡፡

በዓሉ ያለምንም የጸጥታ ችግር እንዲከበር ከማድረግ አኳያ የተሠሩ የቅድመ ዝግጅት ሥራዎችን አስመልክተው የኦሮሚያ ክልል አስተዳደርና ፀጥታ ቢሮ እና የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን በጋራ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡

በመግለጫቸውም÷ በዓሉ ሰላማዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ የፌደራል፣ የአዲስ አበባ ከተማ እና የኦሮሚያ ክልል የፀጥታ አካላት በጋራ እየሠሩ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

የኦሮሚያ አስተዳደርና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ ኮሚሽነር ጀነራል ከፍያለው ተፈራ እንደገለጹት÷ የክልሉ የፀጥታ ኃይል ጥበቃው ውጤታማ እንዲሆን የሚያስችል ቴክኖሎጂ ተግባራዊ ያደርጋል፡፡

ቴክኖሎጂው በዓሉ በሚከበርባቸው የአዲስ አበባ እና ቢሾፍቱ ከተሞች ከፀጥታ ኃይል ውጪ የሆኑ ችግሮችን መቆጣጠር የሚያስችል መሆኑን ገልጸዋል፡፡

የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር አራርሳ መርዳሳ በበኩላቸው÷ ህብረተሠቡ ከፀጥታ አካላት ጎን በመቆም የተለመደ ትብብሩን እንዲያደርግ ጠይቀዋል።

በቤተልሔም መኳንንት

 

Exit mobile version