የሶማሊያው ፕሬዚዳንት ሐሰን ሼክ ሞሃሙድ ለስራ ጉብኝት አዲስ አበባ ገቡ Melaku Gedif 2 years ago አዲስ አበባ ፣ መስከረም 18 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የሶማሊያው ፕሬዚዳንት ሐሰን ሼክ ሞሃሙድ ለይፋዊ የስራ ጉብኝት አዲስ አበባ ገብተዋል። ፕሬዚዳንቱ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ አቀባበል አድርገውላቸዋል። በቆይታቸውም በሁለትዮሽ እና በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ምክክር ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል። በፍሬህይወት ሰፊው