አዲስ አበባ፣ መስከረም 16፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) እ.ኤ.አ በ1992 የባርሴሎና ኦሎምፒክ በ10 ሺህ ሜትር ሴቶች ውድድር ለአፍሪካ የመጀመሪያውን የወርቅና የብር ሜዳልያ ያስገኙት ኢትዮጵያዊቷ የአሁኑ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ደራርቱ ቱሉ እና ደቡብ አፍሪካዊቷ ኤሊና ማየር የመጀመሪያ የኦሊምፒክ ድላቸውን ባጣጣሙበት ባርሴሎና ከተማ ከ30 ዓመት በኋላ በዛሬው እለት ተገናኝተዋል።
የስፖርት ቱሪዝምና የባርሴለሎና ኦሊምፒክ 30ኛ ዓመቱን ለማክበር በተዘጋጀ መርሃ ግብር ላይ ነው ጀግኖቹ በድጋሚ ከፌዴሬሽኑ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
የአፍሪካ ኩራት የሆነችው አትሌት ደራርቱ ቱሉ፥ በኦሎምፒክ በሴቶች 10 ሺህ ሜትር ለአፍሪካ የመጀመሪያውን የወርቅ ሜዳልያ በማስገኘት ታሪክ ሰርታለች።