Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

መስቀል ኢየሱስ ክርስቶስ የሰውን ልጅ መውደዱን ህይወቱን በመስጠት ፍቅርን የገለፀበት በዓል ነው- ከንቲባ አዳነች አቤቤ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 16፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) መስቀል ኢየሱስ ክርስቶስ የሰውን ልጅ ሁሉ ያለዘር፣ ያለቀለም፣ ያለፆታ፣ ያለሀይማኖትና ያለልዩነት መውደዱን ህይወቱን በመስጠት ወደር የማይገኝለትን ፍቅርን የገለፀበት በዓል መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ፡፡

ከንቲባዋ ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።

መስቀል ድንቅ ሃይማኖታዊ  ስርዓት፣ እሴትና ታይቶ የማይጠገብ ትውፊታዊ ይዘትና ተፈጥሯዊ መስህብ   ገፅታዎች የተላበሰ የሀገር መገለጫና ኩራት ከሆኑ በዓላት አንዱ መሆኑንም ነው የገለጹት።

መስቀል ፍቅር፤ የፍቅር፣ የሰላምና የአብሮነት በዓል መሆኑን ጠቅሰው፥ የመስቀል ደመራ በዓል የጨለማው በብርሃን መሸነፍ ማሳያም ነው ብለዋል።

ይህንን በዓል በፍቅር፣ እርስበእርስ በመተሳሰብ ለዘላቂ ሰላም መረጋገጥ በመስራት፣ ጀግኖችን በማክበር፣ ደጀንነትን የበለጠ በማረጋገጥ፣ አንድነትን በማጽናት እንደ ደመራው ደምቀን ጨለማ በሆነብን ሁሉ ላይ እያበራን በአሽናፊነት እንቀጥል ሲሉም መልዕክተ አስተላልፈዋል።

 

Exit mobile version