Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የወላይታ ብሔር የዘመን መለወጫ የ”ጊፋታ” በዓል እየተከበረ ነው

አዲስ አበባ፣ መስከረም 15፣2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአንድነት፣ የሠላም እና የአብሮነት ማብሰሪያ የሆነው የወላይታ ብሔር የዘመን መለወጫ የ”ጊፋታ” በዓል በወላይታ ሶዶ በድምቀት እየተከበረ ነው፡፡

በብሔሩ ዘንድ ከአሮጌው ወደ አዲሱ ዘመን መሸጋገሪያ ብስራት ተደርጎ የሚቆጠረው የጊፋታ በዓል የማጠቃለያ መርሐ ግብር በወላይታ ሶዶ ሁለገብ ስታዲየም በመከበር ላይ ይገኛል፡፡

በበዓሉ ላይ በርካታ ቁጥር ያላው ሕዝብ የተገኘ ሲሆን፥ ታዳሚዎቹ የበዓሉ መገለጫ በሆኑ ባህላዊ አልባሳት ደምቀው በጋራ እያከበረው ይገኛል፡፡

በዓሉ ወደ አዲስ ዘመን መሸጋገሪያ፣ የአንድነትና ሠላም እንዲሁም የአብሮነት ማብሰሪያ ተደርጎም በብሔሩ ተወላጆች ዘንድ ይታመናል፡፡

በመሆኑም በአሮጌው ዘመን የተፈጠሩ ቁርሾና ቂም ልባዊ በሆነ ዕርቅና ወንድማማችነት በማደስ የሚቀበሉት በዓል በመሆኑ የይቅርታና የሰላም በዓል በመባም ይታወቃል፡፡

በዓሉን ምክንያት በማድረግ በተዘጋጀ የፎቶ ኤግዚቢሽን የተለያዩ ባህላዊ እሴቶችም ለዕይታ ቀርበዋል፡፡

በበዓሉ ላይ ሚኒስትሮች፣ በሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር የሚመራ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች፣የተለያዩ ብሔር ብሔረሰቦች ተወካዮች እና በርካታ ቁጥር ያላቸው የአከባቢው ማህበረሰብ ተሳትፈዋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version