Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ መስኮች ያሰለጠናቸውን ከ700 በላይ ተማሪዎችን አስመረቀ

 

አዲስ አበባ ፣ መስከረም 14 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ ለ14ኛ ጊዜ የሕክምና ዘርፍን ጨምሮ በተለያዩ መስኮች ያስተማራቸውን ከ700 በላይ ተማሪዎች አስመረቀ።

 

በምረቃ ስነ ስርዓቱ ላይ የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ጽህፈት ቤት ኃላፊ ዶክተር ሁሴን ቃሲም፣ የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ዶክተር በሽር አብዱላሂ፣ የተመራቂ ተማሪዎች ቤተሰቦች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል ።

 

ዩኒቨርሲቲው በዛሬው ዕለት 704 ተማሪዎችን ያስመረቀ ሲሆን ከተመራቂዎች መካከል 428ቱ በሕክምና ዘርፍ የመጀመሪያ ዲግሪ የተማሩ መሆናቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

 

የተቀሩት በትምህርት አመራር፣ በኢዱኬሽናል ማኔጅመንት፣ ሶሺዮሎጂ ፣ ማኔጅመንት እና አካውንቲንግ የትምህርት ዘርፎች ትምህርታቸውን የተከታተሉ እና የሁለተኛ ዲግሪ ተመራቂዎች እንደሆኑ ተገልጿል።

 

Exit mobile version