የሀገር ውስጥ ዜና

በ2014 ዓ.ም ለተጨማሪ 5 ሚሊየን ዜጎች የንፁህ መጠጥ ውኃ ማቅረብ መቻሉን የውኃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ገለጸ

By ዮሐንስ ደርበው

September 23, 2022

ሚኒስቴሩ በ2015 በጀት ዓመት ዕቅድ ላይ ከተጠሪ ተቋማቱና ከክልል ውኃና ኢነርጂ ቢሮዎች ጋር በባሕርዳር ከተማ እየተወያየ ነው፡፡

የውኃና ኢነርጂ ሚኒስትር ሀብታሙ ኢተፋ በውይይቱ ላይ እንደገለጹት÷ ባለፈው ዓመት ብቻ ለተጨማሪ አምስት ሚሊየን ዜጎች የንፁህ መጠጥ ውኃ ማቅረብ ተችሏል።

የትናንቱ ስኬት ለነገ መነሻችን ነውና የ2015 በጀት ዓመት ዕቅዳችንን በጋራ በመከወን የበለጠ ውጤት ማስመዝገብ ይገባል ሲሉ አሳስበዋል፡፡

በንፁህ መጠጥ ውኃ እጥረት ሴቶች ረዢም ርቀት ለመጓዝ እየተገደዱ መሆናቸውን ጠቁመው÷ ባዮ ጋዝን፣ የፀሐይ ኃይልንና ማገዶ ቆጣቢ ምድጃዎችን በስፋት በማቅረብ የእናቶችን ድካምና ጫና መቀነስ እንደሚገባ በአጽንኦት ገልጸዋል፡፡

በሙሉጌታ ደሴ