የሀገር ውስጥ ዜና

አቶ ደመቀ መኮንን ከቱርክ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጋር ተወያዩ

By Melaku Gedif

September 23, 2022

አዲስ አበባ፣ መስከረም 13፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ከቱርክ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሜቭሉት ካቩሶግሉ ጋር ተወያዩ፡፡

ሚኒስትሮቹ በኒውዮርክ እየተካሄደ ከሚገኘው 77ኛው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ ጎን ለጎን ነው የተወያዩት፡፡

በውይይታቸውም በኢትዮጵያ እና ቱርክ መካከል ያለውን የሁለትዮሽ ግንኙነት ይበልጥ ማጠናከር በሚችሉባቸው ጉዳች ዙሪያ መምከራቸው ተገልጿል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!