አዲስ አበባ፣ መስከረም 12፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢፌዴሪ የሪፐብሊካን ጥበቃ ኃይል ለመካኒሳ መስማት የተሳናቸው ትምህርት ቤት ተማሪዎች ግማሽ ሚሊየን ብር የሚገመት የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ አድርጓል።
የሪፐብሊካን ጥበቃ ኃይል የጤና አገልግሎት ኃላፊ ኮሎኔል ሙሉጌታ ተፈራ ድጋፉን ለተማሪዎችና ለወላጆች አስረክበዋል።
በመርሐ ግብሩ የሪፐብሊካን ጥበቃ ኃይል አመራሮች የመካኒሳ መስማት የተሳናቸው ትምህርት ቤት መምህራን፣ ተማሪዎችና ወላጆቻቸው ተገኝተዋል።
ኮሎኔል ሙሉጌታ ተፈራ ፥ የሪፐብሊኩ ዘብ ለሀገር ህልውና መጠበቅ ከሚያደርገው መስዋዕትነት ባሻገር የህዝብ አጋርና አጋዥ ሠራዊት መሆኑንም በተግባር እያሳየ ነው ብለዋል።
በዚህም ከዚህ ቀደም የአቅመ ደካሞችን ቤት የማደስና ሌሎች የበጎ አድራጎት ተግባራትን ሲያከናውን እንደነበር ጠቅሰው ፥ በቀጣይም በቻልነው አቅም የበጎ ፈቃድ ሥራዎችን እናጠናክራለን ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
የሪፐብሊካን ጥበቃ ኃይል ፅህፈት ቤት ኃላፊው ኮሎኔል ዓለማየሁ ሙለታ በበኩላቸው፥ መስማት ለተሳናቸው ተማሪዎችና ለአቅመ ደካሞች ድጋፍ በማድረግ የህዝብ ሠራዊትነቱን በተግባር ማሳየቱን ይቀጥላል ሲሉም አረጋግጠዋል።
የትምህርት ቤቱ ርዕሰ መምህር ሙሴ ዓለማየሁ ፥ የሪፐብሊካን ጥበቃ ሃይል ላደረጉት ድጋፍ በተማሪዎችና በትምህርት ቤቱ ማህበረሰብ ሲወሳ የሚኖር በአስፈላጊ ወቅት የተደረገ መሆኑን ገልጸዋል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!