የሀገር ውስጥ ዜና

120 አዳዲስ የአንበሳ አውቶብሶች ወደ መዲናዋ ገቡ

By Meseret Demissu

March 18, 2020

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 9፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) 120 አዳዲስ የአንበሳ አውቶብሶች ወደ ከተማዋ ገብተዋል።

እነዚህ አዳዲስ አውቶብሶች መጨናነቅን በመቀነስ የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመከላከል የሚደረጉ ጥረቶችን ለመከላከል ያግዛል ተብሏል።

ከገቡት ውስጥ 70 አውቶብሶች ዛሬ ወደ ስራ የገቡ ሲሆን ቀሪዎቹም በቀጣይ ቀናት ወደ ስራ እንደሚገቡ ከከተማ አስተዳደሩ ከንቲባ ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል