አዲስ አበባ፣ መስከረም 11፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ትምህርት ሚኒስቴር ለመከላከያ ሠራዊት ከ210 ሚሊየን ብር በላይ ጥሬ ገንዘብ እና የንፅህና መጠበቂያ ቁሳቁስ ድጋፍ አድርጓል፡፡
ድጋፋ የተደረገው በትምህርት ሚኒስቴርና ተጠሪ ተቋማቱ ነው፡፡
ድጋፉን የተረከቡት የመከላከያ ሚኒስትር ዴኤታ ማርታ ሉዊጂ÷ ትምህርት ሚኒስቴር እና ተጠሪ ተቋማቱ ላደረጉት ድጋፍ አመስግነዋል፡፡
የትምህርት ሚኒስቴር ዴኤታ ሳሙኤል ክፍሌ ድጋፉን ባስረከቡበት ወቅት ባደረጉት ንግግር÷ ከድጋፉ ባለፈ መከላከያን በማዘመን ረገድ በጋራ እየሠሩ እንደሚገኙ ገልጸዋል፡፡
በቤተልሔም መኳንንት
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!