አዲስ አበባ፣ መስከረም 11፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ ለሚኩራ ክፍለ ከተማ የሚኖሩ የትግራይ ተወላጅ ሴቶች ለጀግናው መከላከያ ሠራዊት ከ3 ነጥብ 3 ሚሊየን ብር በላይ ግምት ያለው የስንቅ ድጋፍ አስረከቡ፡፡
በስንቅ ዝግጅቱ ላይ የተሳተፉ ሴቶች እንደገለጹት÷ ስንቅ ማዘጋጀት ብቻ ሳይሆን አሸባሪው የህወሓት ቡድንን ለመደምሰስ በሚደረገው ትግል በማንኛውም ቦታና ጊዜ ሁሉ ከጀግናው የመከላከያ ሠራዊት ጎን እንሰለፋለን፡፡
መላው የትግራይ ሕዝብ እና ተወላጅም ለርሃብ እና ለችግር የዳረገውን የሽብር ቡድን ከመከላከያ ሠራዊት ጎን በመሰለፍ ለመጨረሻ ጊዜ ሊያስቆመው ይገባል ማለታቸውን የአዲስ አበባ ኮሙኒኬሽን ቢሮ መረጃ አመላክቷል፡፡
የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ዋና ሥራ አስፈፃሚ ጥላሁን ሮባ እንደተናገሩት ክፍለ ከተማው በዛሬው ዕለት ብቻ ከሠራዊቱ ጎን መቆሙን ለማሳየት 3 ነጥብ 3 ሚሊየን ብር ግምት ያለው÷ 20 ሰንጋዎች፣ 20 የበግ ሙክቶች፣ ደረቅ ምግብ፣ የዱቄትና ዘይትን ጨምሮ ለሠራዊቱ አገልግሎት የሚውሉ ሌሎች ድጋፎችን አስረክቧል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!