አዲስ አበባ፣ መስከረም 10፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) አሜሪካ በዓለም ላይ ቀዳሚዋ የጦርነት ምንጭ ከመሆን መታቀብ እንዳለባት የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ዋንግ ዌንቢን ተናገሩት፡፡
ቃል አቀባዩ ይህን ያሉት አንድ ሪፖርት አሜሪካ ከፈረንጆቹ 1991 ጀምሮ እስከ አሁን ድረስ በሌሎች ሀገራት ጉዳይ 251 ጊዜ ወታደራዊ ጣልቃ-ገብነቶችን አድርጋለች የሚለውን መረጃ ይፋ ማድረጉን ተከትሎ ነው፡፡
እንደ ሪፖርቱ፥ ከፈረንጆቹ 1978 ጀምሮ አሜሪካ 469 ጊዜ በሀገራት ጉዳይ ላይ ወታደራዊ ጣልቃ-ገብነቶችን ፈጽማለች፡፡
ሪፓርቱን ያወጣው የአሜሪካዊው ጋዜጠኛ ቤንጃሚን ኖርተን መረጃውን ይፋ ያደረገው÷ የአሜሪካን ምክር ቤት የምርምር አገልግሎት መረጃን ጠቅሶ መሆኑን ሲጂቲ ኤን ዘግቧል፡፡
የቻይናው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ዋንግ ዌን ቢን፥ አሜሪካ በታሪኳ ካሳለፈችው 240 በላይ ዓመታት 16 ዓመታትን ብቻ ጦርነት ውስጥ ጣልቃ ሳትገባ በሠላም ማሳለፏን ጠቁሟል፡፡
አሜሪካ ከቀዝቃዛው ጦርነት በኋላ ለሰባት ጊዜ ወታደራዊ ወረራ መፈጸሟም ነው የተገለጸው፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!