አዲስ አበባ፣ መጋቢት 9፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ጂቡቲ በኮሮና ቫይረስ የተያዘ ሰው የተገኘባት ሌላኛዋ የአፍሪካ ቀንድ ሀገር መሆኗ ተገለፀ።
በቫይረሱ የተያዘው ግለሰብ ከአራት ቀን በፊት ጂቡቲ የደረሰ የስፔን ልዩ ሀይል አባል ሲሆን በትናንትናው ዕለትም ምርመራ ተደርጎለት በቫይረሱ መያዙ ተረጋግጧል።
ስፔናዊው ግለሰብ ከጂቡቲ ዜጋ ጋር እንዳልተገናኘ የሀገሪቱ ጤና ሚኒስቴር አስታውቋል።
አሁን ላይም በለይቶ ማቆያ ይገኛል ብሏል ሚኒስቴሩ።
ከጂቡቲ በተጨማሪም በዛንዚባር በቫይረሱ የተያዘ የመጀመሪያው ሰው የተገኘ ሲሆን፥ በኬንያ እና በታንዛኒያ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር መጨመሩ ተነግሯል።
ምንጭ፦ ሬውተርስ