አዲስ አበባ፣ መስከረም 10፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የዩናይትድ ካፒታል ግሩፕ በኢትዮጵያ በተፈጥሮ ጋዝ ፍለጋና ልማት ላይ የመሰማራት ፍላጎት እንዳለው አስታወቀ፡፡
የኢፌዴሪ የማዕድን ሚኒስትር ኢንጂነር ታከለ ዑማ፥ በጆርዳን ልዑል አባስ ቤን አሊ ቤን ናይፍ በተመራው የዩናይትድ ካፒታል ግሩፕ ልኡካን ቡድን ጋር በተፈጥሮ ጋዝ ኢንቨስትመንት ላይ መወያየታቸውን ገልፀዋል።
ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት በነዳጅና የተለያዩ ማዕድናት ሥራላይ የተሰማራው ይህ ኩባንያ በኢትዮጵያ በተፈጥሮ ጋዝ ፍለጋና ልማት ላይ የመሰማራት ፍላጎት ማሳየቱን አንስተዋል፡፡
አክለውም ፥ ተግባራዊ እንቅስቃሴ ለመጀመር ከልዑኩ ጋር ከስምምነት መደረሱን ነው ያስታወቁት።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!