Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ፕሬዚዳንት ሣኅለወርቅ ዘውዴ በዓለም አቀፍ ደረጃ ትምህርት ለሁሉም መዳረስ እንዳለበት ተናገሩ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 10፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ፕሬዚዳንት ሣኅለወርቅ ዘውዴ በዓለም አቀፍ ደረጃ ትምህርት ለሁሉም መዳረስ እንዳለበትና ለጋራ ተጠቃሚነት የጋራ ኃላፊነት መውሰድ እንደሚገባ ተናገሩ።

ፕሬዚዳንት ሣኅለወርቅ በትምህርት ለውጥ ላይ በሚመክረው ጉባዔ ላይ በበይነ-መረብ መልዕክት አስተልለፈዋል፡፡

በመልዕክታቸውም ለጋራ ተጠቃሚነት የጋራ ኃላፊነት መውሰድ እንደሚገባ አጽንኦት ሰጥተዋል።

ለዚህም የጋራ የሆነ ስምምነት ወይም ማዕቀፍ እንደሚያስፈልግ መጥቀሳቸውን በተመድ የኢትዮጵያ ቋሚ መልዕክተኛ አምባሳደር ታዬ አፅቀሥሳሌ አስታውቀዋል።

አያይዘውም የውሳኔ አሰጣጥ ሥርዓት ሲለወጥ ትምህርት ቤቶች እንደ ልዩ ተቋም ይጠበቃሉም ነው ያሉት።

በትምህርት ለውጥ ላይ በሚመክረው ጉባኤ የዘርፉ ባለሙያዎች፣ ዓለም አቀፍ ተቋማት፣ የሀገራት መሪዎች፣ ሲቪክ ማህበራትና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል።

በጉባኤው ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን፣ በተመድ የኢትዮጵያ ቋሚ መልዕክተኛ አምባሳደር ታዬ አፅቀሥላሴ፣ የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ እንዲሁም የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር መለስ ዓለም ተካፍለዋል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version