Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የሶማሌ ክልል ዳያስፖራዎች የምክክር መድረክ መካሄድ ጀመረ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 9፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የሶማሌ ክልልና የክልሉ ተወላጅ ዳያስፖራ የጋራ ምክክር መድረክ በጅግጅጋ ከተማ መካሄድ ጀምሯል፡፡

በምክክሩ ላይ የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ፅህፈት ቤት ኃላፊ ዶክተር ሁሴን ሃሺ ቃሲምን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች እንዲሁም ከተለያዩ ሀገራት የተውጣጡ የክልሉ ተወላጅ ዳያስፖራ አባላት፣ ባለሃብቶች፣ ምሁራን፣ የሀገር ሽማግሌዎችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

በየዓመቱ በሚካሄደው የጋራ ጉባዔ÷ የክልሉ ዳያስፖራዎች በክልሉ እየተከናወነ ስላለው የኢንቨስትመንት፣ የመሰረተ ልማት፣ የሰላምና ፀጥታ እንዲሁም የብልጽግና ጉዞ እና ዘርፍ ላይ ተወያይተዋል፡፡

በመድረኩ የተገኙት የዳያስፖራ አባላትና ባለሀብቶች በክልሉ እየተካሄደ በሚገኘው የኢንቨስትመንት ልማት ሥራ ላይ እንደሚሳተፉ ጠቅሰዋል፡፡

በተለይም በኢንዱስትሪ መሰረ ልማት ማጠናከር ላይ የኢንቨስትመንት ተሳትፎ እንደሚያደርጉ መግለጻቸውን ከክልሉ ኮሙኒኬሽን የተገኘው መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version