Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ተመድ የአውሮፓ ኅብረት በሩሲያውያን ላይ የጣለውን የቪዛ እገዳ ነቀፈ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 9፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የሩሲያ ጎብኚዎችን ቪዛ የሚከለክለው አዲሱ የአውሮፓ ኅብረትን አሠራር የተመዱ ዋና ጸሃፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ በበጎ ጎኑ እንዳልተመለከቱት አር ቲ ዘገበ፡፡

ክልከላው በዩክሬን እና ሩሲያ መካከል የዘለቀው ግጭት ሲረግብ እንደሚነሳ ያላቸውን ተሥፋ ገልጸዋል፡፡

ዋና ጸሃፊው ክልከላው የሩሲያውያኑን መብት የሚጥስ ነውም ብለዋል፡፡

አንቶኒዮ ጉቴሬዝ እገዳው በአውሮፓ ኅብረት እና በሩሲያ መካከል ያለው ግንኙነት መበላሸቱን የሚያመላክት መሆኑን ነው የተናገሩት።

በዚህ ወር ኅብረቱ ከሩሲያ ጋር የነበረውን የቪዛ ሥምምነት ማቆሙ ተሠምቷል።

ይህን ተከትሎም አንዳንድ የኅብረቱ አባል ሀገራት የጎብኚ እና የንግድ ቪዛ መስጠት አቁመዋል ነው የተባለው፡፡

ኢስቶኒያ፣ ላቲቪያ፣ ሉቴኒያ እና ፖላንድ ሩሲያውያን ከሌሎች ሀገራት በተሰጡ የሼንገን ቪዛ ወደ ሀገራቱ እንዳይገቡ መከልከላቸውን አስታውቀዋል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version