Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የግዳን ወረዳ ነዋሪዎች እና የድሬዳዋ ከተማ ለሀገር መከላከያ ሰራዊት የአይነት ድጋፍ አደረጉ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 9፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር እና የሰሜን ወሎ ዞን ነዋሪዎች ግንባር ለሚገኘው የሀገር መከላከያ ሰራዊት የአይነትና የስንቅ ድጋፍ አድርገዋል፡፡

በሰሜን ወሎ ዞን የግዳን ወረዳ ነዋሪዎች በሰሜን ወሎ ግዳን ግንባር ለሚገኘው የሀገር መከላከያ ሰራዊት የስንቅ እና ሌሎች ድጋፎችን ግንባር ድረስ በመገኘት ድጋፍ አድርገዋል።

የአካባቢው ነዋሪዎች ጦርነቱ በድል እስከሚጠናቀቅ ድረስ ድጋፋቸውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ተናግረዋል።

በተመሳሳይ የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ለሰራዊቱ ከ6 ነጥብ 8 ሚሊየን ብር በላይ ግምት ያላቸው፥ የበሬ፣ ፍየል እንዲሁም ስንቅና ቁሳቁስ ያካተተ ድጋፍ የአስተዳደሩ ከፍተኛ አመራሮች በቢሾፍቱ ተገኝተው አስረክበዋል፡፡

በሁለተኛው ዙር የተደረገው ድጋፍ ከአስተዳደሩ ባለሀብቶችና ነዋሪዎች እንዲሁም ከመንግስት ሰራተኞች የተሰበሰበ ሲሆን÷ ድጋፉ እስከ ጦርነቱ ፍጻሜ እንደሚቀጥል በድጋፍ ርክክቡ ወቅት ተገልጿል።

እንዲሁም በጉባላፍቶ ወረዳ የድሀ ወዲህ ቀበሌ ነዋሪዎች በግንባር ለሚገኘው የሀገር መከላከያ ሠራዊት የስንቅ ድጋፍ አስረክበዋል።

ነዋሪዎቹ በአላውኃ ግንባር  ተገኝተው “ጀግኖቻችን በርቱ ፤ ምን ጊዜም ከጎናችሁ ነን”  ሲሉ ማበረታታቸውን የወረዳው ኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት መረጃ ያመላክታል፡፡

በተጨማሪም የላልይበላ ከተማ ነዋሪዎች ለሀገር መከላከያ ሠራዊት የእርድ ሰንጋዎችን ድጋፍ ማድረጋቸውን የሰሜን ወሎ ዞን ኮሙኒኬሽን መረጃ አመላክቷል፡፡

በለይኩን ዓለም ፤ ተጨማሪ መረጃ ከድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ኮሙኒኬሽን

Exit mobile version