የሀገር ውስጥ ዜና

አምባሳደር ሐሰን ኢብራሂም የሹመት ደብዳቤያቸውን ለፕሬዚዳንት አል ሲሲ አቀረቡ

By Meseret Awoke

September 19, 2022

አዲስ አበባ፣ መስከረም 9፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በግብጽ የኢትዮጵያ አምባሳደር ሆነው የተሾሙት አምባሳደር ሐሰን ኢብራሂም ሙሳ የሹመት ደብዳቤያቸውን ለግብጹ ፕሬዚዳንት አብዱል ፈታህ አል ሲሲ አቀረቡ።

ፕሬዚዳንት አል ሲሲ አዲስ አምባሳደሮችን በካይሮ አቀባበል ያደረጉላቸው ሲሆን፥ በቆይታቸው ስኬታማ እንዲሆኑ ተመኝተዋል።

ግብፅ ከሀገራቱ ጋር በሁሉም መስኮች ያላትን የሁለትዮሽ ግንኙነት ለማጠናከር ፍላጎት እንዳላትም ነው የገለጹት።

ፕሬዚዳንቱ የኢትዮጵያን ጨምሮ የ13 ሀገራት አዲስ አምባሳደሮችን የሹመት ደብዳቤ ተቀብለዋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!