Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ፕሬዚዳንት ሳኅለወርቅ በንግስት ኤልሳቤጥ 2ኛ ህልፈት የተሰማቸውን ሐዘን በለንደን በመገኘት ገለጹ

አዲስ አበባ ፣ መስከረም 8፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ፕሬዚዳንት ሳኅለወርቅ ዘውዴ በእንግሊዟ ንግስት ኤልሳቤጥ 2ኛ ህልፈት የተሰማቸውን ሐዘን በለንደን በመገኘት ገለጹ።

ፕሬዚዳንቷ በንግስቷ ህልፈት በኢትዮጵያ ህዝብ ስም ሀዘናቸውን ለመግለፅ ለንደን ሂትሮ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የቤኪንግሃም ቤተመንግስት ተወካዮች እና የኢትዮጵያ ኤምባሲ የስራ ሀላፊዎች አቀባበል አድርገውላቸዋል።

ለንግሥቲቱ በተዘጋጀ የሀዘን መግለጫ መዝገብ ላይም ሀዘናቸውን ገልፀዋል።

ንጉስ ቻርለስ ሶስተኛ በቤኪንግሃም ቤተመንግስት ባዘጋጁት የእራት ግብዣ ላይም ተገኝተዋል።

በ96 አመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩት ንግስት ኤልሳቤጥ 2ኛ ፥ ነገ የቀብር ስነስርዓታቸው ይፈፀማል።

በቀብር ስነስርዓታቸው ላይም ፕሬዚዳንት ሳኅለወርቅ ዘውዴን ጨምሮ የበርካታ ሀገራት ርዕሰ ብሄሮች፣ መሪዎች እና የንጉሣውያን ቤተሰቦች ይገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል።

Exit mobile version