የሀገር ውስጥ ዜና

የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት ለአፋር ክልል 14 ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረገ

By Mikias Ayele

September 18, 2022

አዲስ አበባ፣ መስከረም 8፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ)የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለአፋር ክልል 14 ሚሊየን ብር የሚገመት የአይነት ድጋፍ አድርጓል፡፡

ድጋፉን የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ምክትል አፈ ጉባኤ ወይዘሮ ሎሚ በዶ ሰመራ ተገኝተው ለክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ አስረክበዋል፡፡

ምክትል አፈ ጉባኤዋ ÷ የተደረገው ድጋፍ የተወካዮች ምክር ቤት ሴት ተመራጮች በክልሉ በጦርነት ለተፈናቀሉ ወገኖች ያሰባሰቡት መሆኑን ገልጸዋል።

ድጋፉ 14 ሚሊየን ብር የሚገመት የተለያዩ አልባሳት፣ፓስታ፣ ዘይትና በቆሎን ያካተተ መሆኑን ነው የተናገሩት፡፡

ወይዘሮ ሎሚ በዶ አፋር ክልል ሰመራ ከተማ ሲገቡ ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባን ጨምሮ ከፍተኛ የክልሉ የስራ ሃላፊዎች አቀባበል ያደረጉላቸው መሆኑን ኢዜአ ዘግቧል፡፡