አዲስ አበባ፣ መስከረም 7፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የማዕከላዊ ጎንደር ዞን ሕዝብ ለመከላከያ ሠራዊት ከ2 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር በላይ ግምት ያላቸው 105 የእርድ እንስሳት ድጋፍ አድርጓል፡፡
የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ ወርቁ ኃይለማርያም ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደገለጹት፥ አሸባሪው ህወሓት ኢትዮጵያን ለማፍረስ እየሠራ ያለውን ዕኩይ ምግባር ለመመከት የዞኑ ሕዝብ በወኔ እና በከፍተኛ ቁጭት እየሠራ ነው፡፡
በቀጥታ ከሚደረገው ድጋፍ በተጨማሪ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች የዘማች ቤተሰቦችን የግብርና ሥራዎች በመከወን ደጀንነታቸውን እያሳዩ ነው ብለዋል፡፡
የሰሜን ጎንደር ዞን ምክትል አስተዳዳሪ እና የግንባሩ የሕዝብ ድጋፍ እና ሎጅስቲክስ አስተባባሪ ደብረወርቅ ይግዛው በበኩላቸው÷ የሽብር ቡድኑን ወረራ ለመቀልበስ የኢትዮጵያ ሕዝብ ድጋፉን እንዲያጠናክር ጠይቀዋል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!