የሀገር ውስጥ ዜና

የፌደራል ፖሊስ ወንጀል መከላከል ጠቅላይ መምሪያ የእውቅና ሽልማት መርሐ-ግብር አካሄደ

By Alemayehu Geremew

September 17, 2022

አዲስ አበባ ፣ መስከረም 7 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ወንጀል መከላከል ጠቅላይ መምሪያ የእውቅና ሽልማት መርሐግብር በሚሊኒየም አዳራሽ አካሄደ።

በመርሐ-ግብሩ የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጄነራል ደመላሽ ገብረ ሚካኤል፣ የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል፣ የኢትዮ- ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈጻሚ ፍሬህወት ታምሩን ጨምሮ የተለያዩ የስራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል።

እውቅናና ሽልማቱ የተሰጠው በሀገሪ ወንጀል መካከል ተግባር በአመራርነትና፣ በአዛዥነትና በጀግንነት የላቀ ውጤት ላስመዘገቡ አካላት መሆኑ ተመላክቷል።

እውቅናና ሽልማቱ የተበረከተው በጠቅላይ መምሪያው 24 ክፍሎችና እና በስሩ ለሚገኙ 6 ተጠሪ ክፍሎች መሆኑን ኢዜአ ዘግቧል።