Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በሶማሌ ክልል የኩፍኝ መከላከያ ክትባት መሰጠት ተጀመረ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 6፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በሶማሌ ክልል የኩፍኝ መከላከያ ክትባት መርሐ ግብር መሰጠት ተጀምሯል፡፡

የክትባት ዘመቻው በሀገር አቀፍ ደረጃ በ22 ወረዳዎች የሚካሄድ ሲሆን በሶማሌ ክልል 11 ወረዳዎች  ክትባቱ እንደሚሰጥ ነው የተገለፀው፡፡

ዘመቻው በሚካሄድባቸው አራት ቀናት ወላጆች ልጆቻቸውን በማስከተብ ሀላፊነታቸውን እንዲወጡ ጥሪ መቅረቡን የሶማሌ ክልል መገናኛ ብዙሀን ዘግቧል።

Exit mobile version