ፋና ስብስብ

ኢትዮጵያዊው ወጣት 220 ሜትር ርዝመት ያለው የአንገት ልብስ ሰራ

By Shambel Mihret

September 16, 2022

አዲስ አበባ፣ መስከረም 6፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአፍሪካ ድንቃድንቅ መዝገብ በኢትዮጵያ 220 ሜትር ርዝመት ያለውን የአንገት ልብስ መዘገበ፡፡

በወጣት ወንድምአገኝ ዳምጠው የተዘጋጀው እና 220 ሜትር ርዝመት ያለው የአንገት ልብስ በኢትዮጵያ የመጀመሪያው ነው ተብሏል።

በዓለም ላይ ትልቁ የአንገት ልብስ 29 ሺህ ሜትር እንደሚደርስና በደቡብ አፍሪካ እንደተሰራ ተገልጿል፡፡

የአፍሪካ ድንቃድንቅ መዝገብ መስራች አሸናፊ አለም እንደገለጹት÷ ሁለተኛው በህንድ ሶስተኛው ደግሞ በኖርዌይ እንዲሁም አራተኛው በካምቦዲያና አምስተኛው በኢትዮጵያ ይገኛል ብለዋል።

የወንድማገኝ ዳምጠው የአንገት ልብስን ለየት የሚያደርገው የአባቶችን የሽመና ጥበብ በመጠቀም የተሰራ መሆኑን ጠቅሰው÷ በስፋትም የዓለም ክብረ ወሰን የያዘ መሆኑን ተናግረዋል።

የጥላቻ ንግግሮችን የምንዋጋው እንደዚህ አይነት ፈጠራዎችን በማበረታታትና እንደ ወንድምአገኝ ያሉ ጀግና ሰዎችን ወደፊት በማምጣትና እውቅና በመስጠት መሆኑንም አመላክተዋል።

የአንገት ልብሱን ለመስራት 10 ቀናት እንደፈጀበት የሚናገረው ወንድምአገኝ ዳምጠው÷ የአካባቢው ወጣቶች ያግዙት እንደነበር ገልጿል።

በአለምሰገድ አሳዬ