አዲስ አበባ ፣ መስከረም 6 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ህወሓት መቀሌ በሚገኘው የዓለም ምግብ ፕሮግራም መጋዘን ውስጥ የፈጸመው የነዳጅ ዝርፊያ የድርጅቱን ስራ እንዳከበደበት ዋና ዳይሬክተሩ ዴቪድ ቤስሊ ገለጹ።
በተመድ የኢትዮጵያ ቋሚ መልዕክተኛ አምባሳደር ታዬ አፅቀሥላሴ በትዊተር ገጻቸው ባሰፈሩት ፅሁፍ ዋና ዳይሬክተሩ በፀጥታው ምክር ቤት ስብሰባ ላይ ቡድኑ የፈጸመው ዝርፊያ ድርጅቱ በትግራይ በሚያከናውነው ስራ ላይ ትልቅ እንቅፋት እንደፈጠረ መግለጻቸውን ጠቅሰዋል።
አያይዘውም ድርጅቱ በሰሜኑ የኢትዮጵያ ክፍል ለሚያከናውነው የሰብአዊ ድጋፍ ነዳጅ፣ ድጋፍ እና ተንቀሳቅሶ መስራት እንፈልጋለን ማለታቸውን አስታውቀዋል።
አሸባሪው ህወሓት ባለፈው ነሐሴ ወር መቀሌ በሚገኘው የዓለም ምግብ ፕሮግራም ድርጅት ግቢ ውስጥ በመግባት 570 ሺህ ሊትር ነዳጅ መዝረፉ ይታወሳል።
ይህን ተከትሎም የዓለም ምግብ ፕሮግራም ሰብአዊ ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው ወገኖች ተዘዋውሮ ድጋፍ ለማድረግ መቸገሩን በተደጋጋሚ ሲገልጽ ቆይቷል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!