አዲስ አበባ፣ መስከረም 5፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ፕሬዚዳንት ፑቲን ቻይና በዩክሬኑ ጦርነት ላይ እያራመደች ያለውን ሚዛናዊና ገለልተኛ አቋም አድንቀው አሜሪካ በታይዋን ላይ እያሳየች ያለችውን ኢፍትሃዊ አካሄድ ኮነኑ፡፡
የሩስያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ከቻይናው አቻቸው ፕሬዚዳንት ሺ ጂንፒንግ ጋር በኡዝቤኪስታን ሳማርካንድ ዛሬ በተካሄደው የሻንጋይ የትብብር ድርጅት ( ኤስሲኦ) ስብሰባ ላይ ተገናኝተው ተወያይተዋል።
በውይይታቸውም÷ ፕሬዚዳንት ፑቲን የቻይናው አቻቸው ፕሬዚዳንት ሺ ከዩክሬኑ ጦርነት ጋር በተያያዘ እያሳዩት ያለውን ሚዛናዊ አቋም አድንቀዋል፡፡
ከዩክሬኑ ቀውስ ጋር በተያያዘ “ወዳጅ ሀገር ቻይና እያራመደች ላለችው ሚዛናዊ አቋም ትልቅ ክብር አለን“ ነው ያሉት ፕሬዚዳንት ፑቲን፡፡
ፑቲን ከታይዋኑ ግጭት ጋር በተያያዘም፥ አሜሪካ በሁለቱ ወገኖች ጉዳይ ላይ የምታደርገውን ጣልቃ ገብነት አውግዘው ከቻይና ጎን እንደሚቆሙ በግልጽ ተናግረዋል፡፡
ሁለቱ ፕሬዚዳንቶች የሩስያ -ዩክሬን ጦርነት ከተጀመረ በኋላ ፊት ለፊት ተገናኝተው ሲወያዩ የአሁኑ የመጀመሪያ ጊዜያቸው መሆኑን ሮይተርስ በዘገባው አውስቷል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!